ፕሮፌሰር ጄይላን ወልዬ ሁሴንን የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዚዳንት ተድርጎ ተሾሟል።
HU FM 91.5 RADIO ክፍት የነበረውን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ቦታ ላይ ኃላፊ ለመመረጥ የተደረገውን ውድድር መሰረት በማድረግ የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ቦርድ ከግንቦት 21 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ፕሮፌሰር ጄይላን ወልዬ ሁሴንን የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟል። በዚሁ መሰረት ፕሮፌሰር ጄይላን ወልዬ ዛሬ በአዲሱ ቢሮአቸው ተገኝተው ስራቸውን ጀምረዋል